[et_pb_section fb_built=”1″ _builder_version=”3.22″][et_pb_row _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ sticky_enabled=”0″]
አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ አሳሳቢ ላለቻቸው ወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ የማፈላለግ ኃላፊነት የጣለችባቸው አዲሱ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን በኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መነጋጋር እንደሚፈልጉ ለፎሬን ፖለሲ መጽሔት ነግረውታል፡፡
በአደባባይ ዲስኩሮች ወታደሮቹ የኢትዮጵያን መሬት ለቀው እንደሚወጡ ቢነገርም መሬት ላይ ያለው ሐቅ ግን እሱን እንደማያመለክት የሚናገሩት አዲሱ ሹመኛ፣ እንዲያውም እየተጠናከሩ እንደሚገኙ በመጠቆም ብስጭታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጄፍሪ ፌልትማን ከመሪዎቹ የሚያደርጉት ንግግር አስቸጋሪ እንደሚሆን የተናገሩ ሲሆን፣ በተለይ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የሚደረገው ንግግር ይበልጥ አስቸጋሪ ቢሆንም ሁኔታዎችን ለማርገብ ከሁሉም ጋር የመነጋገርን አስፈላጊነት አንስተዋል፡፡
አዲሱ ሹመኛ ‹‹ውስብስብ እና የሚዋልል ምስቅልቅል የማያጣው›› ሲሉ የገለጹትን የምሥራቅ አፍሪቃ ቀጣና ሰላም ለመመለስ የትግራይን ችግር መፍታት ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡ ከትግራይ ችግር በመቀጠል ደግሞ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ችግር መፍታት እንዲሁም በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን ውጥረት ማርገብ ተከታይ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የ62 ዓመቱ ጄፍሪ ፌልትማን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሆነው በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው አንቶኒ ብሊንከን የተሾሙት ባለፈው ሳምንት ዐርብ ነበር፡፡
[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]