አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 9፣ 2014 ― የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችው ወልድያ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር መዋሏን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል፡፡
መከላከያ በትናንትናው ዕለት ማምሻውን በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን መቆጣጠሩን ያስታወሰው አገልግሎቱ፣ አሁን ደግሞ ወልድያ ከተማን ጨምሮ ሐራ፣ ጎብየ፣ ሮቢትን እና ቆቦን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ብሏል፡፡