Sunday, September 22, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የመሥራት ፍላጎት ላላቸው አገራት ግብዣ አቀረበች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ታኅሣሥ 7 2014 ― አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የመሥራት ፍላጎት ያላቸውን አገራት በሙሉ እንደምትቀበል የገለጸችው በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛዋ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በኩል ነው፡፡

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ለሁለት ቀናት በቱርክ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን፣ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ‹‹ምንም ዐይነት ወታደራዊ መፍትሄ›› የለውም ባሉት የኢትዮጵያ ግጭት ላይ መምከራቸውን የቱርክ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ምክክሩን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው በቱርክ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ፌልትማን በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ማረጋጋጥ የጋራ ግብ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን አስፍሯል፡፡

ጄፍሪ ፌልትማን በቱርክ በነበራቸው ቆይታ ካናገሯቸው ባለስልጣናት መካከል በቱርክ የአፍሪካ ቀንድ ምክትል ኃላፊ ሰዳት ኦናል ይገኙበታል፡፡  

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ባለፉት ቀናት ከቱርክ በተጨማሪ የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት እና ግብጽ እንደጎበኙ መነገሩ አይዘነጋም፡፡ ሆኖም ወደ ተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት እና ግብጽ ስላደረጉት ጉዞ መረጃ አልወጣም፡፡

አሁን ኢትዮጵያን በተመለከተ ወደ ሦስት አገራት ጉዞ ያደረጉት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን፣ የትግራይ ጦርነትን በተመለከተ ለመምከር በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ ሲመላለሱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img