አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 6፣ 2014 ― ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በቁጥጥር ስር የዋለው የተራራ ኔትወርክ መስራች እንዲሁም ላለፉት 27 ቀናት ደብዛው ጠፍቷል የተባለው የአሐዱ ራዲዮ አርታኢ ክብሮም ወርቁ ያሉበት ይፋ እንዲደረግ የጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ነው።
ከታሰረ ስድስት ቀናት ያስቆጠረው ታምራት ነገራ ቀድሞ ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደተወሰደ የተነገረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ የት እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ማወቅ እንዳልቻሉ እየገለጹ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር ተለቋል የተባለው የአሐዱ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ዜና አርታኢ ክብሮም ወርቁን ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ከወር በፊት የታሰረው ክብሮም ወርቁ በአዲስ አበባ ፖሊስ ከእስር መፍታቱ ቢገለፅም፣ ላለፉት 26 ቀናት ቤተሰቦቹ የት እንዳለ እንደማያውቁ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያሳውቅም፣ ቤተሰቦቹ በበኩላቸው ክብሮም ከ26 ቀናት በፊት በፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቀ ቢወሰንለትም እስካሁንም ያለበትን እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።
ሁለቱም የሚዲያ ባለሞያዎች የት እንደሚገኙ ይፋ እንዲደረግ የጠየቀው ኢሰመኮ፣ የሚመለከታቸው አካላት በኢትዮጵያ ተጥሎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ መተግበሩን እንዲቆጣጠሩም ብሏል።