Wednesday, October 9, 2024
spot_img

‘ሸኔ’ን የማስተዋወቅ ሥራ ሲሠሩ ነበሩ የተባሉ የሚዲያ ባለሞያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 6፣ 2014 ― በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በሽብርተኝነት የተፈረጀው የተፈረጀውን በመንግስት ሸኔ የሚባለውን እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራውን ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበሩ የተባሉ የሚዲያ ባለሞያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢቢሲ የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል።

ከሚዳ ቀኝ ወረዳ እስከ ኬንያ ድረስ ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው ቡድኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበሩ የተባሉት አንደኛ ተጠርጣሪ አሚር አማን የአሶሺየትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ፣ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ቶማስ እንግዳ የካሜራ ባለሞያ እና ሦስተኛ ተጠርጣሪ አዲሱ ሙሉነህ የኤፍቢሲ ጋዜጠኛ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ባለሞያዎቹ የቡድኑን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከታትሎ በመቅረጽና ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃዎችን በማሰባሰብ ኬንያ ለሚገኘው እና የአሶሽየትድ ፕረስ የምሥራቅ አፍሪካ ተወካይ ነው ለተባለው ግብጻዊ ዜግነብ ላለው ካሊድ ካዚሃ መላካቸው በማስረጃ መረጋገጡንም ፖሊስ አስታውቋል ነው የተባለው።

ተጠርጣሪዎቹ ከአዲስ አበባ በመንቀሳቀስና የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ቀርጸው እንዲመጡ ከግብጻዊው ጋዜጠኛ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጉዳዩ ዓለም አቀፍ በሆነው አሶሽየትድ ፕረስ እንዲተላለፍ ማድረጋቸውንም ተጠቁሟል።

ወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበትና የተለያዩ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በወቅቱ አዲስ አበባ ተከባለች፤ ህወሓትና ሸኔ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሱ ነው፤ በሚል ወሬ የሚያናፍሱበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀልበስ ወደ ግንባር በዘመቱበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ሆን ብለውና አስበውበት ህዝቡን ለማሸበር ቀረጻው በዓለም አቀፍ ሚዲያ እንዲተላለፍ በማድረጋቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስረድተዋል መባሉን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ተጠርጣሪዎቹ አሸባሪው ቡድን እንዲታወቅ የሚዲያ ተልዕኮ ተቀብለው ህዳር 16 ቀን ወደ ስፍራው በማቅናት እስከ ህዳር 18፣ 2014 ቀረጻ በማከናወን እና ፕሮዳክሽን በመስራት ከላኩ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው እና በስራ ገበታቸው ህዳር 19፣ 2014 በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።

የሚዲያ ባለሞያዎቹን እስር በተመለከተ ሥማቸው የተጠቀሰው አሶሽየትድ ፕረስ እና መንግስታዊው ኤፍቢሲ የሰጡት ማብራሪያ የለም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img