Thursday, November 28, 2024
spot_img

የገና እና ፋሲካ ባዛር ለማዘጋጀት በ110 ሚሊዮን ብር ያሸነፈው ድርጅት ኮንትራት ተሰረዘ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 2፣ 2014 ― መጪውን የገና እና ቀጣዩን ፋሲካ በዓላት ለማዘጋጀት ከኤግዚቢሽን ማዕከል በ110 ሚሊዮን ጨረታ ያሸነፈው ቤታሆን ኤቨንትስ ኮንትራቱ የተሰረዘው ቅድመ ክፍያ ባለማስገባቱ ነው።

ቤታሆን ኤቨንስትስ ለሁለቱ መጪ በዓላት ያስገባው 110 ሚሊዮን ብር ቀድሞ ከነበረው 65 በመቶ ጭማሪ ያሳየ በታሪክ ከፍተኛ የተባለ የጨረታ ገንዘብ እንደነበር ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

አሁን ኮንትራቱ የተሰረዘበት ቤታሆን፣ ዓምና በሚያዝያ ወር ሊያዘጋጅ የነበረው የኢትዮጵያ ባንኮች እና ኢንሹራንስ ኤክስፖን ሊያዘጋጅ አቅዶ በኮሮና ምክንያት ሳይሳካለት ቀርቷል።

የኤግዚቢሽን ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ታደሰ እንዳሉት ከሆነ ድርጅቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚከፈተው የገና ባዛር ከገንዘቡ 60 በመቶውን እንዲያስገባ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ በማስገባት ቢጠበቅም ሊያስገባ አልቻለም።

የኤግዚቢሽን ማዕከል ለቤታሆን ኤቨንትስ ገንዘቡን እንዲያስገባ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ የተጠናቀቀው ትላንት እኩለ ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

ጉዳዩን የሚታዘቡ ሰዎች ኤቨንት አዘጋጁ ቀድሞም ቢሆን የተጋነነ እንደነበር መናገራቸው በዘገባው ተጠቅሷል።

የቤታሆን ኤቨንትስን ኮንትራት የሰረዘው ኤግዚብሽን ማዕከል፣ ባዛሩን በራሱ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳለው ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img