Sunday, October 6, 2024
spot_img

መዐዛ መሐመድ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 2፣ 2014 ― ሮሃ ቲቪ በተባለ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ በፕሮግራም አቅራቢነት የምትሠራው መዐዛ መሐመድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏ ተነግሯል፡፡

መዓዛ በቁጥጥር ስር የዋለችው፣ በዛሬው እለት ከመኖሪያ ቤቷ ትፈለጊያለሽ ተብላ መሆኑን አዲስ ዘይቤ የተሰኘ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡  

መዐዛ በምን ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለች የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ከዚህ ቀደም ዐባይ ሚዲያ በተባለ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ በምታዘጋጃቸው ቃለ ምልልሶች የምትታወቀው መዐዛ መሐመድ፣ ሮሃ ቲቪ የተባለውን ብዙኃን መገናኛ የከፈተችው በቅርቡ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ባለፉት ቀናት በተመሳሳይ ኡቡንቱ በተሰኘ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ የሚሠራው እያስጴድ ተስፋዬ እና የተራራ ኔትወርክ መስራቹ ታምራት ነገራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡  

 

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img