Sunday, October 6, 2024
spot_img

ታምራት ነገራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 1፣ 2014 ― ተራራ ኔትዎርክ በተባለ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛ ፖለቲካዊ አስተያየቶችን የሚያቀርበው ታምራት ነገራ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱን የሚሠራበት ተራራ ኔትወርክ አስታውቋል፡፡

ታምራት ነገራ በተወሰደበት ወቅት የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቱ እና ቢሮውን በመፈተሽ ለመረጃ ይፈለጋሉ ያሏቸውን የሚዲያ ዕቃዎች በሙሉ ወስደዋል ነው የተባለው፡፡

ተወሰዱ የተባሉት ዕቃዎች በዋናነት፣ ላፕቶፕ፣ ኮምፒተሮች፣ መቅረፀ ድምፅ፣ ፋላሽ ሚሞሪ፣ እና ሌሎች የሚዲያ መገልገያ መሣሪያዎች መሆናቸው ተዘርዝሯል፡፡

ታምራት ነገራ በምን ምክንያት እንደታሰረ የተገለፀ ነገር ባይኖርም፣ ከሰሞኑ አክቲቪስት እና የፖለቲካ አስተያየት ሰጪው እያስጴድ ተስፋዬ መታሠሩን ተከትሎ ታምራት ነገራም መታሠር አለበት በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግበት ቆይቷል፡፡

ታምራት ነገራ በቀድሞ አዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነት የሚታወቅ ሲሆን፣ የጋዜጣውን መዘጋት ተከትሎ አስር ዓመት ገደማ በአሜሪካ ስደት ላይ ቆይቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ወደ አገር ቤት የተመለሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img