[et_pb_section admin_label=”section”]
[et_pb_row admin_label=”row”]
[et_pb_column type=”4_4″][et_pb_text admin_label=”Text”]
አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― ከቀናት በፊት በሰሜን ሸዋ አካባቢ በንጹሐን ላየይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል መቀመጫ ባህር ዳር ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በአምስት ባንኮች ላይ የዘርፊያ መከራ ተደርጎ የሰዎች ሕይወት ማለፉም ተነግሯል፡፡በከተማው የዝረፊያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ማለትም 2 የኦሮሚያ የህብረት ሥራ ባንክ፣ 1 የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ 1 የቡና ባንክ እና 1 የወጋገን ባንክ ቅርጫፎች መሆናቸውን የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡በዚሁ የዝርፊያ ሙከራ ወቅት የአንደኛው ባንክ ጥበቃ ሁለት ወጣቶችን ተኩሶ መግደሉ ነው የተነገረው፡፡ በባህር ዳር ከተማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 14 በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንኮች የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡
[/et_pb_text][/et_pb_column] [/et_pb_row] [/et_pb_section]