Friday, November 22, 2024
spot_img

የኬንያ መንግሥት ዳዳብና ካኩማ የስደተኛ ጣቢያዎችን እንደማይዘጋ ተመድ ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― የኬንያ መንግሥት ዳዳብና ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፖችን አይዘጋም ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም ከፍተኛ ኮሚሽነር ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ወር ኬንያ የአገር ውስጥ ደኅንነቴ አደጋ ላይ ወድቋል በሚል ዳዳብና ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን ልትዘጋ መሆኑን አሳውቃ ነበር። ስደተኞች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በሩዋንዳና በቡሩንዲ ውስጥ ያለባቸውን ችግር ለማየት ጉብኝት ያደረጉት ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትላንትናው እለት ሩዋንዳ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ‹‹ከኬንያ መንግሥት ጋር መልካም ውይይት አድርጊያለሁ›› ብለዋል። ‹‹የኬንያ መንግሥት እነዚህን ጣቢያዎች አይዘጋም። የኬንያ መንግሥት የሚፈልገው መፍትሄ ነው። ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚቻል ማየት ይሻል›› ብለዋል ግራንዲ።የስደተኞች ኮሚሽን ስለሁለቱ ጣብያዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚተነትን ዕቅድ ለኬንያ መንግሥት ማስገባቱንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።ኮሚሽነሩ አክለውም ‹‹የኬንያ መንግሥት ስደተኛ ተቀባይነቱን ይቀጥልበታል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን ወደፊት ምን ይሆናል የሚለውን ማወቅ ይፈልጋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እየመከርን ነው›› ማለታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡ ባለፈው ወር የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 400 ሺሕ ስደተኞች የሚያስተናግዱትን ሁለቱን መጠለያዎች መንግሥት እንዳይዘጋ ማገዱ ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img