አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 30፣ 2014 ― ኤርትራ እስካሁን ድረስ ለዜጎቿ የኮሮና ክትባት መስጠት አለመጀመሯን ያስታወቀው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ነው፡፡
በበይነ መረብ በተደረገ ገለጻ ላይ ይህንኑ የተናገሩት የማዕከሉ ባልደረባ የሆኑት ጆን ኬንጋሶንግ፣ ኤርትራ ከአፍሪካ አህጉር የኮሮና ክትባትን ለዞጎች መስጠት ባለመጀመር ብቸኛዋ አገር ብትሆንም አሁንም ተስፋ አንቆርጥም ብለዋል፡፡
ወርልዶ ሜትር እንደተባለው ዓለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ሪፖርት መመዝገቢያ ድረ ገጽ፣ በኤርትራ እስካሁን ድረስ 7 ሺሕ 533 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 62 ሰዎች ሞተዋል፡፡