Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ለሁለት አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች ፍቃድ ለመስጠት ያወጣችው ዓለም አቀፍ ጨረታ ተዘጋ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰጪዎች ፍቃድ ለመስጠት ያወጣው ጨረታ በዛሬው እለት መዘጋቱን ያስታወቀው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።በዛሬው እለት በተካሄደው የጨረታ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ሰነድ ያስገቡ ኩባንያዎች ሥም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።በዚህም ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በተባለ ተቋም ስር ሳፋሪኮም ከኬንያ፣ ቮዳፎን ከብሪታኒያ፣ ቮዳኮም ከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ እና ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን በጥምረት እንዲሁም ኤ.ቲ.ኤን ከደቡብ አፍሪካ እንደሚገኙበት ነው የገለጸው።ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትሰጣቸው ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፍቃዶች አሸናፊዎች ባለሥልጣኑ በተረከባቸው የጨረታ ሰነዶች ላይ የሚያከናውነውን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ግምገማዎች ካጠናቀቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑም ተነግሯል።ባለሥልጣኑ የአገሪቱን የቴሌኮም አገልግሎት በብቸኝነት ከያዘው ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ለሁለት ኩባንያዎች ፍቃድ ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ ያወጣው ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ነበር።ይህን ተከትሎም ኅዳር 18፣ 2013 ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ አይዘነጋም።ሂደቱ መንግሥት የገጠመውን የውጭ መንዛሬ ዕጥረት ለመፍታት እና ውድድርን ለመፍጠር ካቀዳቸው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች አንዱ መሆኑንም ጠቅሶ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img