Saturday, November 23, 2024
spot_img

ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይ ሳምንት የ5ጂ ኔትወርክ ሙከራ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 28፣ 2014 ― መንግሥታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይ ሳምንት የ5ጂ ኔትወርክ ሙከራ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተነግሯል፡፡

ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው ኩባንያው ይህንኑ አገልግሎት ይፋ ለማድረግ የቻይናውን ሁዋዌ ኩባንያ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ላለፉት ሁለት ወራት ዝግጅት ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

እጅግ ፈጣን እንደሆነ የሚነገርለት የ‹አምስተኛ ትውልድ› ወይም 5ጂ ኔትወርክ በዓለም ላይ ጥቅም ላይ ከዋለ ዋል አደር ብሏል።

በቀጣይ ሳምንት የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክ ሙከራ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል የተባለው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከ50 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የሚገልጽ ሲሆን፣ አሉኝ ከሚላቸው ከ50 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች መካከል ከ 48 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ከ23 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይነገራል፡፡

ኩባንያው ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ የሚነገርለትን የ4ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ይህንኑ የ4ጂ አገልግሎት ከጀመረበት አዲስ አበባ ከተማ ውጪ በተለያዩ የክልል ከተሞች በማስፋፋት ሒደት ላይ መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል፡፡

የ4ጂ ተከታይ የሆነው የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክ፣ የቀጣዩ ትውልድ የሞባይል በይነ መረብ ግንኙነት ሲሆን፣ እጅግ በጣም ፈጣን ዳታ የማውረድ እና የመጫን አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ ኔትወርኩ የሬዲዮ ሰፔክትረም በመጠቀም እጅግ በጣም ብዙ መሣሪያዎችን በአንድ ጊዜ የሞባይል ኢንተርኔቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img