Thursday, November 28, 2024
spot_img

በጠ/ሚ ዐቢይ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ኮምቦልቻ እየገሠገሠ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 25፣ 2014 ― በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደ ኮምቦልቻ ከተማ እየገሠገሠ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ገልጿል።

እንደ ኮሚኒኬን አገልግሎት ከሰሞኑ በሕወሓት የተያዙ አካባቢዎችን ነጻ ያወጣው የፀጥታ ኃይል በጋሸና ግንባር ቀውዝባና ጭላ ከተሞችና አካባቢያቸው ከሕወሓት ኃይል ነጻ ያወጣ ሲሆን፣ በወረኢሉ ግንባር በተደረገው ኦፐሬሽን ደግሞ አጅባር፣ ተንታ እና ዶባ ከተሞችና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል። በተያያዘም በከሚሴ ግንባር ማጀቴን፣ ጭረቲን፣ ከሚሴን፣ ርቄን፣ ወለዲን፣ አልቡኮ ከተሞችን እና የቃሉ ወረዳን አብዛኛውን ክፍል በመቆጣጠር ወደ ኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ይገኛል ብሏል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አክሎም አስቀድሞ ነጻ በወጡት በምሥራቅ፣ በምዕራብና በመሐል ግንባር በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች መንግሥታዊ አስተዳደር ተመልሶ በመደራጀት ሥራውን መጀመሩንም አስታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img