Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአገር መከላከያ ኃላፊው የሕወሓት መሪዎች በሕይወት ስለመኖራቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 24፣ 2014 ― የሕወሓት መሪዎች በሕይወት ስለመኖራቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው የገለጹት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ኃላፊ የሆኑት ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ናቸው፡፡

ሌተናል ጄነራል ባጫ ይህን የገለጹት፣ ቢቢሲ የሕወሓት ኃይሎች ባወጡት መግለጫ በአማራ ክልል ተይዘው ከነበሩ ቦታዎች በታክቲካዊ ውሳኔ ወጥተናል ማለታቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ወቅት ነው፡፡

ኃላፊው በሰጡት ምላሽ ‹‹ታዲያ ምን እንዲሉ ነው የሚጠበቀው›› ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ በመመለስ፣ ‹‹እዚህ የደረሱት በአቅማቸው በጉልበታቸው አይደለም፣ በላኳቸው ሰዎች ጉልበት እና አቅም ነው›› ብለዋል፡፡ የሕወሓት ኃይሎች መግለጫውን ማውጣታቸው ‹ጌቶቻቸውን ለማስደሰት›› የተደረገ ነው ብለውታል፡፡

አያይዘውም ‹‹ለምን እንደድሮው ጻድቃን የሚባለው ወይም የእነሱ ሰዎች ወጥተው መግለጫ አይሰጡም›› ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፣ ‹‹ስለመኖራቸውም እጠራጠራለሁ›› ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

የሕወሓት መሪዎችን በተመለከተ ከሰሞኑ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕወሓት የያዛቸውን አካባቢዎች ማስለቀቁን ማሳወቁን ተከትሎ፣ ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ ሰኞ ኅዳር 20፣ 2014 ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ እና ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም ያሉትን ፎቶግራፍ የለጠፉ ቢሆንም፣ አንዳቸውም በቅርብ ቀናት በመገናኛ ብዙኃን አልቀረቡም፡፡

አንድ ዓመት የተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ ቀጥሎ የአገር መከላከያ ሠራዊት ላሊበላን ጨምሮ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው የተባለለትን ጋሸናን መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ኃላፊ የሆኑት ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ እንደገለጹት ደግሞ መከላከያ በዛሬው እለት ዐርብ ‹‹ባቲ፣ ደሴ እና ኮምቦልቻን አንድ ላይ ይያዛሉ የሚል ግምት አለ››።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img