Sunday, July 7, 2024
spot_img

ኢሰመኮ እና የመንግሥታቱ ድርጅት በአማራ እና አፋር ክልሎች የመብት ጥሰት ምርምራ ለማድረግ በንግግር ላይ ናቸው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 24፣ 2014 ― በጥቅምት ወር መገባደጃ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ምርመራቸውን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተመድ) የሰብዓዊ መብት ጽ/ቤት በአማራ እና አፋር ክልሎች የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ ምርምራ ለማድረግ በንግግር ላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ይህንኑ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከአል ዓይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በተመከተ ‹‹የመጨረሻ ስምምነት ላይ ስላልደረስን እርግጠኛ መልስ አሁን ለመስጠት አልችልም፡›› ያሉት ዶክተር ዳንኤል፣ ‹‹ግን ተመሳሳይ አይነት የጣምራ ምርመራና ሪፖርት ለማከናወን ግን ከተመድ ጋር ምክክር ተጀምሯል›› ብለዋል፡፡

ኢሰመኮ እና የተመድ የሰብአዊ መብት ጽሕፈት ቤት በቅርቡ ይፋ ባደረጉት ምርመራ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ኃይል፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ በአንድ ወገን እንዲሁም የትግራይ ልዩ ኃይል፣ የትግራይ ሚሊሻ እና ሌሎች ቡድኖች በሌላ ወገን ሆነው በጦርነቱ ተሳትፈው ፈጽመዋቸዋል ያሏቸውን ጥሰቶችን ዘርዝሯል፡፡

ሪፖርቱን በተመለከተ መንግሥት የተወሰኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ሲቀበለው፣ ሕወሃት በበኩሉ ከሪፖርቱ ቀድሞ መውጣት አስቀድሞ እንደማቀበለው አስታውቆ ነበር፡፡

ሕወሓት ሪፖርቱን አልቀበልም ማለቱን ተመለከተ ምላሽ የሰጡት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ ሕወሓት አልቀበልም ‹‹ከመነሻው ጀምሮ በሂደቱ ውስጥም አልሳተፍም በማለትም ጭምር›› በማለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምርመራ ሂደቱ ላይም ሳይሳተፍ የቀረው በኢሰመኮ ላይ እምነት የለኝም የሚል ምክንያት በማቅረብ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡

አጋጣሚው ‹‹አሳዛኝ›› ሲሉ የገለጹት ዶክተር ዳንኤል፣ ‹‹ሪፖርቱ ከወጣ በኋላ ደግሞ የሪፖርቱን ሚዘናዊነት ተመልክተው ይቀበሉታል የሚል ተስፋ ነበረኝ፤ አሁንም ምናልባት በጥሞና ሪፖርቱን ካነበቡት ሊቀበሉ የማይችሉበት ምክንያት እኔ አለ ብዬ አላምንም›› ሲሉ ተስፋቸውን ተነግረዋል፡፡

አንድ ዓመት የተሸገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ጦርነት የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን የወጡ ሪፖርቶች አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img