Thursday, November 28, 2024
spot_img

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 22፣ 2014 ― የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ባደረገው የጋራ ውይይት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ እንዲሆኑ ውሳኔ መተላለፉን አስታውቋል።

ትምህርት ቤቶቹ ዝግ በሚሆኑበት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3፣ 2014 ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች “ለሃገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ” ተብሏል።

በተጨማሪም ትምህርት ቤቶቹ ዝግ በሚሆኑበት ወቅትም ያልተሰበሰቡ የዘማች ሰብል መሰብሰብና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት እደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡

በዚህ ሂደት ትምህርት የቆመባቸው ቀናቶች በሙሉ ት/ቤቶች በሚያወጡት የማካካሻ መርሃግብር መሰረት እንዲካካስ እንደሚደረግም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img