Monday, September 23, 2024
spot_img

ሳዑዲ ዐረቢያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ኦሚክሮን በተሰኘው የኮቪድ ልውጥ የተያዘ ሰው ማግኘታቸውን ሪፖርት አደረጉ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 23፣ 2014 ― ሳዑዲ ዐረቢያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በአዲሱ ኦሚክሮን የተሰኘ ሥያሜ በተሰጠው የኮሮና ቫይረስ ልውጥ የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት አድርገዋል፡፡

የሳዑዲ ዐረቢያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ አገሪቱ ያገኘችው በአዲሱ የኮቪድ ልውጥ የተያዘ ግለሰብ በወል ካልተጠቀሰ የሰሜን አፍሪካ አገር የተነሳ ነው፡፡ ይህን ተከትሎም በቫይረሱ የተጠቃው ግለሰብ እና ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎች ለብቻ እንዲገለሉ ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬት የመጀመሪያውን በኦሚክሮን የተያዘ ሰው ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች፡፡ የአገሪቱ የዜና አገልግሎት በአዲሱ ቫይረስ መያዟ የተለየቸው ሴት ከአፍሪካ አገር ወደ ኤሜሬቶች የገባች መሆኗን ጠቅሷል፡፡

ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮቪድ ልውጥ ቫይረስ በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ከተገኘ በኋላ ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ተደርጓል።

ልውጡ ኦሚክሮን ዓለምን በከፍተኛ አደጋ የጣለ የጤና ስጋት ነው የተባለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በከፍተኛ ሁኔታ የመተላለፍ ሁኔታና እንደገና የመያዝ አደጋም ደቅኗል።

በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በደቡብ አፍሪካ የተገኘው ልውጥ በሃገሪቱ ውስጥ በሁሉም ግዛቶች በኮሮና ቫይረስ እየተያዙ ያሉ ሰዎችን ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፡፡

የቫይረሱን መገኘት ተከትሎ እንግሊዝ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካን ጨምሮ አገራት በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎች ደቡባዊ የአፍሪካ ሃገራት ላይ የጉዞ እገዳ ጥለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img