Thursday, October 10, 2024
spot_img

ከሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ታወጀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 22፣ 2014 ― ከሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ መታወጁን ያስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ ነው።

እዙ የሰአት እላፊውን ያወጀው ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል መሆኑን እወቁት ብሏል።

በዚሁ መሠረት በአካባቢዎቹ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታውጇል።

በተጨማሪም ከሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የታወጀውን የሰዓት እላፊ በተመለከተ ወደ አካባቢው የገቡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ፤ እንዲሁም የሰዓት እላፊውን እንዲያስፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛር እንዳስታወቀው ላሊበላን ጨምሮ ጋሸና እና ሌሎችም ከተሞች በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ገብተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img