Saturday, November 23, 2024
spot_img

የሕወሓት ኃይሎች የላሊበላን ከተማ ለቀው መውጣታቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 22 2014 ― የሕወሓት ኃይሎች የላሊበላ ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ቀድሞ በጦርነቱ ሰበብ ከከተማ የሸሹ ሁለት ነዋሪዎች የሕወሓት ኃይሎች ከተማውን ለቀው መውጣታቸውን በስፍራው ከሚገኙ ዘመዶቻቸው መስማታቸውን መናገራቸውን ዘግቧል።

በተመሳሳይ ሬውተርስ ከላሊበላ በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው ግራኝ አምባ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ነግሮኛል እንዳለው፣ የሕወሓታ ታጣቂዎች አካባቢውን ትላንት ለቀው ወጥተዋል።

ከሰሞኑ በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ተባብሶ የቀጠለውን ጦርነት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባር ሆነው መከላከያን እየመሩ ስለመሆናቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አግልግሎት በዛሬው እለት እንዳስታወቀውም፣ ሕወሓት ቁልፍ የጦር ስልታዊ ቦታው አድርጎ ይዞት ነበር የተባለው ጋሸና በመከላከያ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መከላከያ በወልደያና ኮምቦልቻ በወረራቸው አካባቢዎች ያሉት በወረኢሉ ግንባር ኢንቁፍቱ፣ አቀስታ፣ ወረኢሉ ከተሞችን ተቆጣጥሯል የተባለ ሲሆን፣ መዘዞ፣ ሞላሌ እና ሸዋሮቢት በሸዋ ግንባር በመከላከያ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

የአገር መከላከያ ሠራዊት በተመሳሳይ በሕወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበረውን በአፋር ክልል ጭፍራ ከተማን መቆጣጠሩ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img