Saturday, November 23, 2024
spot_img

የኬንያው ኔሽን ሚዲያ ግሩፕ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የኢትዮጵያ ዘጋቢው እንዲለቀቅ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 22፣ 2014 ― በኬንያ ሠፊ ሥርጭት ያለውን የኬንያውን እለታዊ ጋዜጣ ዴይሊ ኔሽን የሚያስተዳድረው ኔሽን ሚዲያ ግሩፕ፣ በአዲስ አበባ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የኢትዮጵያ ዘጋቢው ተስፋዓለም ተክሌ እንዲለቀቅ ጠይቋል፡፡

ኔሽን ሚዲያ ግሩፕ ይህንኑ ጥያቄውን ለኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግልባጭ ደብዳቤ ማስታወቁን በድረ ገጹ ገልጧል፡፡

እንደ ኔሽን ሚዲያ ግሩፕ ከሆነ ዘጋቢው ተስፋዓለም ተክሌ፣ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋለው ጥቅምት 21፣ 2014 ሲሆን፣ ከአራት ቀናት እስር በኃላ የአንድ ሺሕ ብር የገንዘብ ዋስትና ቢፈቅድለትም ሊለቀቅ አልቻለም፡፡

ፖሊስ ተስፋዓለም ተክሌን ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አለው በሚል እንዲሁም ገዢውን ፓርቲ በማብጠልጠል ጠርጥሮ ማሰሩን መናገሩን ሚዲያው አስፍሯል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የተናገሩት የኔሽን ሚዲያ ግሩፕ ኤዲቶሪያል ዳሬክተር ሙቱማ ማቲው፣ የተስፋዓለም ተክሌ ደህንነት እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ፣ ባለልጣናት ተስፋዓለም ተክሌ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እንዲያሳውቋቸው መጠየቃቸው ተመላክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img