አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 21፣ 2014 ― የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ቆይታ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ እና ሌሎች አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎ እነንደሚጠበቅ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ አሜሪካ እና እንግሊዝን ጨምሮ የምዕራብ አገራት ዜጎቻቸውን ኢትዮጵያን ለቃችሁ ውጡ ባሉበት ጊዜ ነው።