አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 21፣ 2014 ― የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ነገ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተነግሯል።
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በነገው እለት አዲስ አበባ ሲደርሱ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት የሚደረገው፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ አሜሪካ እና እንግሊዝን ጨምሮ የምዕራብ አገራት ዜጎቻቸውን ኢትዮጵያን ለቃችሁ ውጡ ባሉበት ጊዜ ነው።