Sunday, October 6, 2024
spot_img

የገለልተኛ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ዶክተር እሌኒ ገብረመድሕንን ከአባልነት አሰናበተ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― ከሰሞኑ ዓለም አቀፍ የሰላም እና ልማት ማዕከል በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አዘጋጅነት በተካሄደ ምስጢራዊ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ታዋቂዋ የኢኮኖሚ ባለሞያ ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባልነታቸው ተሰናብተዋል።

የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የአማካሪ ምክር ቤቱ ትላንት ኅዳር 18፣ 2014 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት ጠንካራ አቋም በጣም ማዘኑን በመግለጽ፣ ግለሰቧ በገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤት አባል ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ውሳኔውን በጽሑፍ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ምንም እንኳን የገለልተኛ ኢኮኖሚ አማካሪዎቹ በግል የራሳቸው የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚችል አስታውሶ፣ ሆኖም አማካሪዎቹ ያቋቋሙት ም/ቤት ህገ ደንብ ግን የምክር ቤቱን አባላት የአማካሪነት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ከየትኛውም ፓርቲም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ነጻ መሆን እንደሚገባቸዉ በግልጽ ያስቀምጣል ብሏል፡፡

በመሆኑም የገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤቱን ውሳኔ መነሻ በማድረግና ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በመንግስትና በህዝብ ታምነው የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ ይሁንታ የሰጠውን መንግስት ቀይሮ የሽግግር መንግስት ስለማቋቋም በግልጽ ምክክር ሲያደርጉ በመገኘታቸው ከዛሬ ኅዳር 19፣ 2014 ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን አሳውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img