Saturday, October 5, 2024
spot_img

ቱርክ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በንግግር በሚፈታበት መንገድ ላይ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አሳወቀች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― ቱርክ በኢትዮጵያ በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት መካከል ያለው ግጭት በንግግር በሚፈታበት መንገድ ላይ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

ይህንኑ የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉድ ቻቩሾግሎ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ መናገራቸውን አናዶሉ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አጎራባች አፋር እና አማራ ክልሎች የተዛመተው በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በንግግር በሚፈታበት መንገድ ላይ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ያሳወቀችው ቱርክ፣ ከወራት በፊት ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ እየሸጠች መሆኗ ተዘግቦ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ከቱርክ ትገዛዋለች የተባለው ‹‹ባይራክታር- TB2›› የተባለው ሰው አልባ አውሮፕላን ሲሆን፣ ከመለዋወጫና ሥልጠና ዋስትና ጋር ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቧም ነበር የተሰማው፡፡

ሆኖም መንግስት ከቱርክ ሊገዛው ነው ስለተባለው ሰው አልባ አውሮፕላን የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img