Sunday, October 6, 2024
spot_img

በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመራው የሰላም እና ልማት ማዕከል ፍቃድ ተሰረዘ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 17፣ 2014 ― በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመራው የሰላም እና ልማት ማዕከል የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ማኅበር ሕጋዊ ፍቃዱን የሰረዘው የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ነው።

የድርጅቱ ፍቃድ የተሰረዘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ለሕወሃት ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ ያመነውን ማንኛውም የሲቪል ማኅበራት ድርጅት ሕጋዊ ፍቃዱ እንዲሰርዝ በአዋጁ የተሰጠው ሥልጣን መሠረት አድርጎ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የሰላም እና ልማት ዓለም አቀፍ ማዕከል ባለፈው እሑድ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ መሪነት በአደባባይ የታወቁ ኢትዮጵያዊያን እና የውጭ አገራት ዲፕሎማቶች የተሳተፉበት በሕወሃት መሪነት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ዙሪያ በምስጢር ውይይት ማድረጉ ይፋ ተደርጎ ነበር።

በውይይቱ ላይ ለተወያዮቹ ማብራሪያ በመስጠት የሕወሃት አባሉና በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት እንተካለን በሚል በአሜሪካ ዋሺንግተን ጥምረት መመስረታቸውን ካስታወቁት ዘጠኝ አካላት መካከል የሆኑት አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ከውጭ አገራት ዲፕሎማቶች መካከል በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ፣ አሜሪካዊቷ ዲፕሎማት ቪኪ ሀድልስተንን ጨምሮ በኢትዮጵያ የአሜሪካ፣ እንግሊዝና አውሮፓ ኅብረት የቀድሞ አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባል የሆኑት ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ዶክተር እሌኒ ገብረመድሕን የተሳተፉ ሲሆን፣ ይኸው የዶክተር እሌኒ ተሳትፎ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች በርካታ ነቀፌታ አዘል አስተያየቶችን አስተናግዷል፡፡ 

ዛሬ የታገደው ውይይቱን ያዘጋጀው የሰላም እና ልማት ማዕከል በሀገር ውስጥ በሰላም ግንባታ፣ ግጭት አፈታት እና እርቅ ዙሪያ እንደሚሠራ በድረ ገጹ ላይ ሠፍሯል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img