Monday, October 7, 2024
spot_img

በአማራ ክልል በሚገኘው መቻከል ወረዳ ሠርግን ጨምሮ ማንኛውንም ድግስ ላልተወሰነ ጊዜ ታገደ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 16፣ 2014 ― በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ የሚገኘው መቻከል ወረዳ ሠርግን ጨምሮ ማንኛውንም ድግስ ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱን አስታውቋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ታደሰ «በአካባቢው ለሰርግና ለሌሎችም ማህበራዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ወጪ ይወጣል፣ ሆኖም አሁን አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ለአገር ህልውና አንዱ እየሞተና እየቆሰለ ባለበት ሰዓት ማንኛውም ለደስታና ፈጠዝያ ተብሎ የሚደረግ ዝግጅት እንዲቋረጥ ተደርጓል ማለታቸውን ዶይ ቨለ ዘግቧል።

አስተዳዳሪው «ምናልባት ልጆቻቸውን መዳር የሚፈልጉ ሰዎች በቤተሰብ ደረጃ በመጠኑ እንዲከናወን እንደሚደረግም» መግለጻቸውን ዘገባው አክሏል።

ከሀዘን ጋር በተገናኘ የሚደረጉ ወጪዎችም እንዲቀነሱና በመጠኑ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏልም ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማቻከል ወረዳ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀመዘምራን መምህር ሰለሞን ጋሻዬ ሰርግና ሌሎች ተመሳሳይ ወጪ የሚጠይቁ ማህበራዊ ጉዳዮች በጊዜያዊነት እንዲቆሙ መወሰኑ ትክክለኛ ነው ብለዋል፡፡

«አገር ጭንቅ ላይ ባለችበት ሰዓት የሚደለቅበትና ዳንኪራ የሚመታበት ሳይሆን ፈጣሪን በፆምና በጸሎት የሚለመንበት ጊዜ ሊሆን እንደሚገባም» አስገንዝበዋል።

በመቻከል ወረዳ የታየው አረአያነት በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲተገበርም መጠየቃቸው ተመላክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img