Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጉቴሬዝ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 16፣ 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ ተፋላሚ አካላት መካከል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ጉቴሬዝ ይህን ጥሪ ያቀረቡት የኮሎምቢያ መንግሥት ከቀድሞው የኮሎምቢያ አብዮታዊ ጦር ኃይሎች ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት አምስተኛ ዓመት መታሰቢያን ለማክበር ኮሎምቢያን በመጎብኘት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

ጉቴሬዝ በኮሎምቢያ ያለው የሰላም ሂደት ኢትዮጵያን ለማዳን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በአገሪቱ ላሉ ተፋላሚ ወገኖች አስቸኳይ ጥሪ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።

ዋና ፀሐፊው ተኩስ አቁም ስምምነቱ “በውይይት ቀውሱን ለመፍታት እና ኢትዮጵያ ለቀጠናው መረጋጋት እንደገና የበኩሏን አስተዋፅዖ እንድታደርግ ያስችላል” ብለዋል።

አንድ ዓመት የተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ መቀጠሉ የሚነገር ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መከላከያን ከጦር ግንባር ለመምራት መዝመታቸው መነገሩ ይታወሳል።

በአንፃሩ ጦርነቱ እንዲቆም በዋነኝነት የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛው ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ኢትዮጵያ ልኮ የማሸማገል እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img