Sunday, September 22, 2024
spot_img

የመንግሥት መደበኛ ሥራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን የኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 15 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባር ተገኝተው አመራር ለመስጠት በመዝመታቸው የመንግሥት መደበኛ ሥራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንባር ተገኝተው ለመከላከያ አመራር እየሰጡ እንደሚገኙ መናገራቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ሌሎች አመራሮችም የህልውና ያሉትን ዘመቻ በመቀላቀል ወደ ግንባር መዝመታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አያይዘውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው በርካቶችን ያነቃቃና በርካቶች እንዲከተሏቸው አድርጓል ብለዋል፡፡

ሰኞ ኅዳር 13፣ 2013 ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ያካሄደውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ተከትሎ መግለጫ የሠጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ‹‹ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ›› በማለት፣ ‹‹ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ›› የሚል መልእክት ሰደው ነበር፡፡

የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው እንደሚከውኑም ገልጸዋል፡፡

አንድ ዓመት የተሻገረው በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ መቀጠሉን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img