Saturday, November 23, 2024
spot_img

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ በሚያካሄደው ጉባኤ የክልሉን ሕገ መንግሥት ያጸድቃል

 

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 14 2014  የምሥረታ ጉባኤውን በቦንጋ ከተማ እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዛሬው እለት የክልሉን ሕገ መንግሥት ያጸድቃል ተብሏል፡፡

 

አዲሱ ክልል በጉባኤው ሕገ መንግሥቱን ከማጽደቁ በተጨማሪ፣ የክልሉን የመጀመሪያ ርዕሰ መስተዳድርም የሚመርጥ ሲሆን፣ በአፈ ጉባኤነት የሚመሩትን ግለሰብም ይሰይማል።

 

ክልሉን ከመሠረቱት ስድስት መዋቅሮች የተወከሉ ሃምሳ ሁለት አባላት ያሉት አዲስ የተቋቋመው የክልሉ ምክር ቤት፣ በዛሬው ጉባኤው የአባላቱን ቁጥር ለመጨመር የወጣውን አዋጅ ጨምሮ ሌሎች ድንጋጌዎችን ያጸድቃል ተብሎ ተጠብቋል፡፡

 

በመስከረም ወር መገባደጃ የሕዝበ ውሳኔ ያደረገው አስራ አንደኛ ሆኖ የተመዘገበው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ከደቡብ ክልል ምክር ቤት የሥልጣን ርክክብ ያደረገው ጥቅምት 24፤ 2014 ነበር፡፡

አስራ አንደኛውን የኢትዮጵያ ክልል የመሰረቱት የካፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

 

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img