Sunday, September 22, 2024
spot_img

አስራ አንደኛው የኢትዮጵያ ክልል የምሥረታ ጉባኤ እና በዓሉን ዛሬ እና ነገ ያካሄዳል

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 13፣ 2014 ― በቅርቡ አስራ አንደኛው የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ የተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ እና ነገ የምሥረታ ጉባኤ እና በዓሉን ያካሄዳል።

በካፋ ዞን መቀመጫ ቦንጋ ከተማ ለሚካሄደው ጉባኤ እና በዓል እንዲታደሙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ትላንት እሑድ ኅዳር 12 ወደ ከተማይቱ መግባታቸው ተነግሯል፡፡

ከክልል ምስረታ ዋዜማ ጀምሮ እንግዶችን የምታስተናግደው የቦንጋ ከተማ አውራ ጎዳናዎቿን በሰንደቅ ዓላማ እና በ“እንኳን ደህና መጣችሁ” መልዕክቶች እንዳሸበረቀች የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም በመንገድ ዳር በርካታ ድንኳኖች የተተከሉ ሲሆን፣ ከድንኳኖቹ በሚወጣ የካፊቾ ባህላዊ ሙዚቃ፤ ህጻናት እና ወጣቶች በጭፍራ ደስታቸውን ሲገልጹ መታየቱንም ዘገባ አክሏል፡፡

በመስከረም ወር መገባደጃ የሕዝበ ውሳኔ ያደረገው አስራ አንደኛ ሆኖ የተመዘገበው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ከደቡብ ክልል ምክር ቤት የሥልጣን ርክክብ ያደረገው ጥቅምት 24፤ 2014 ነበር፡፡

አስራ አንደኛውን የኢትዮጵያ ክልል የመሰረቱት የካፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img