Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሲኤንኤን እና ሬውተርስን ጨምሮ ለአራት ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 10፣ 2014 ― የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ኤን ኤን፣ ቢቢሲ፣ ሬውተርስ እና አሶሺዬትድ ፕረስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ባለሥልጣኑ ለአራቱ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ማስጠንቀቂያ የሰጠው መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ሲል የሚጠራውን እርምጃ መውሰድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያደረገውን ክትትል መሠረት አድርጎ መሆኑን ጠቅሷል።

ባለሥልጣኑ ለመገናኛ ብዙኃኖቹ በጻፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዳመለከተው፣ የተጠቀሱት መገናኛ መገናኛ ብዙኃን የሕወሃትን አላማ የሚደግፍ ዜና እና ትንታኔ ማቅረባቸውን፣ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማስመሰል ዘገባ መስራታቸውን፣ መንግስት የሚሠራውን የሰብአዊ አቅርቦት ማጣጣላቸውን፣ መንግስት ረሐብ እና የአስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል ዘገባ መስራታቸውን እንዲሁም የአገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ማሳጣታቸውን እና በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ጫና ውስጥ እንዲገባ ማድረጋቸውን ገልጿል።

በመገናኛ ብዙኃኑ ታይቷል ያለው ችግር እንዲታረም በመደበኛ እና ኢ መደበኛ ውይይቶች ሙከራ ማድረጉን ያስታወሰው ባለሥልጣኑ፣ ነገር ግን ለውጥ ሊመጣ እንዳልቻለ አመልክቷል።

ባለሥልጣኑ ይህንኑ ተከትሎ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መላኩን ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚህ አግባብ ማስተካከያ ካልተደረገ የኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱበትን ፍቃድ ሊነጥቅ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን፣ በተደጋጋሚ በመንግስት ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበሩ መሆናቸው ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img