Sunday, September 22, 2024
spot_img

የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ተኩስ ማቆም ይቻላል ብለን እናምናለን ሲሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 7፣ 2014 ― የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራይቼል ኦማሞ በኢትዮጵያ ተኩስ ማቆም ይቻላል ብለን እናምናለን ሲሉ በዛሬው እለት ተናግረዋል።

በትግራይ ተጀምሮ አንድ ዓመት የተሻገረውን በፌዴራል መንግሥት እና ህወሓት መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማሸማገል ከሰሞኑ በአፍሪካ ኅብረት የምሥራቅ አፍሪካ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ራይቼል ኦማሞ ይህን የገለጹት፣ በአገራቸው ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት ከአሜሪካ አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር በናይሮቢ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። 

በዋናነት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባተኮረው መግለጫ፣ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ለዚህ ቀውስ መፍትሔ ለማግኘት ኢትዮጵያ ባላት አቅም እናምናለን። ተኩስ ማቆም ይቻላል ብለን እናምናለን” ሲሉ ተናግረዋል። 

አንቶኒ ብሊንከን ከኬንያ አቻቸው ጋር በጋራ መግለጫ ከመስጠታቸው አስቀድሞ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ብሊንክንን ያስተናገዱት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ባለፈው እሁድ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መምከራቸው ይታወቃል።
 
ኡሁሩ የሚመሯት ኬንያ በተመሳሳይ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ የነበሩት የአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማንን አስተናግዳለች።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img