አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 7፣ 2014 ― የመንግሥት ባለሥልጣናት በልዩ ሁኔታ በሚሰጣቸው ካልሆነ ከአገር እንዳይወጡ ክልክላ እንደተጣለባቸው አምባ ዲጂታል ሰምቷል።
በመንግሥት ባለሥልጣናት ተጥሏል የተባለው ከሀገር የመውጣት የክልከላ ትዕዛዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል የተላለፈ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በዚሁ መሠረት የመንግሥት ባለሥልጣናት ከሀገር ለመውጣት ሲፈልጉ በልዩ ሁኔታ ፍቃድ መሰጠቱን የሚገልጽ ፈቃድ ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ወይም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ደብዳቤ መያዝ ይኖርባቸዋል ተብሏል።
በመንግሥት በሽብርተኝነት የተፈረጁት ሕወሓትና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን የደቡብ ወሎ አካባቢዎችን ተቆጣጥረናል ማለታቸውን ተከትሎ በመላው አገሪቱ ከጥቅምት 23፣ 2014 አንስቶ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ መታወጁ ይታወቃል።
what