አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ኅዳር 5፣ 2014 ― የጎረቤት አገር ኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬ እለት አዲስ አበባ ተገኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የተቀበሏቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ የሚል መልዕክት አስፍረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች በተሠራጩ ፎቶ ግራፎች ላይ ኡሁሩ ኬንያታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ ከፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ታይተዋል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካውን የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማንን በናይሮቢ አስተናግደዋል።
ፌልትማን በተመሳሳይ አዲስ አበባ እንደነበሩ ይታወቃል።
የየኡሁሩ ኬንያታ የአዲስ አበባ ጉብኝት በነገው እለት በአገራቸው ከሚቀበሏቸው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክንን ከመቀበላቸው ቀድሞ የተደረገ ነው።