Sunday, September 22, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ ከተማ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የኮቪድ ክትባት በዘመቻ ሊሰጥ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 3፣ 2014 ― በአዲስ አበባ ከተማ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የኮቪድ ክትባት በዘመቻ ሊሰጥ መሆኑን ያስታወቀው የከተማው ጤና ቢሮ ነው፡፡

ቢሮው ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከመጪው ሰኞ ኅዳር 6 እስከ ኅዳር 15፣ 2014 የሚካሄደው የኮቪድ ክትባት ዘመቻ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚሰጥ ነው፡፡

በከተማው በአሁኑ ወቅት ሶስቱ የክትባት አይነቶች ማለትም አስትራዜኒካ፣ ሲኖፋርም እና ጆንሰን ኤንድ ጆንደን እድሜያቸዉ ከ18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ እየተሰጠ መሆኑን ያስታወሰው የጤና ቢሮው፣ ፋይዘር የተሰኘው የኮቪድ 19 ክትባት ወደ ሀገሪቱ በመግባቱ እድሜያቸዉ 12 አመት በላይ ለሆኑ ታዳጊ ወጣቶች እንዲሁም ለአዋቂዎች ሁሉ የሚሰጥ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት ሲባል በጤና ጣቢያዎች፣ በትላልቅ የገበያ ቦታዎች፣ በባንኮች፣ በትራንሰፖርት፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች የተመረጡ ቦታዎች እንደሚሰጥም ጨምሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በክትባት ዘመቻው ላይ የሚሰጡት የኮቪድ 19 ክትባቶች በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና እና ፍቃድ ያገኙ እንዲሁም በመላው ዓለም በሚገኙ ሃገራት በስፋት እየተሰጡ ያሉ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የምግብ እና መዳኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ደህንነታቸው እና ፍቱንነታቸው ተረጋግጦ ፍቃድ አግኝተዉ የሚሰጡ መሆናቸውን እወቁት ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊዮን መሻገሩን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img