Sunday, September 22, 2024
spot_img

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በቅርቡ 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 3፣ 2014 ― ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ በምትገነባው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ በቅርቡ 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ሁሪያ አሊ ናቸው፡፡

ሚኒስትር ደኤታዋ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶችን እያካሄደች መሆኑን በመግለጽ፣ በቅርቡም ከግዙፉ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የሃይል መመንጨት እንደሚጀምር አያይዘው ጠቁመዋል መባሉን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ከተጀመረ አስር ዓመታት ያስቆጠረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሱዳንና ግብፅ ጋር ሲያነታርክ ቆይቷል፡፡ በግድቡ ላይ የሚካሄደው ድርድር መቋጫ ያላገኘ ቢሆንም፣ አሁን ግድቡ ኃይል ወደ ማመንጨቱ ተቃርቧል።

የቀድሞው የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትሩ እና የአሁኑ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ዶ/ር ስለሺ በቀለ የሕዳሴ ግድቡ በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ወራቶች ላይ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀመር ከወራት በፊት ተናግረው ነበር።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የኃይል ማመንጫ ግድቦቿ 4 ሺሕ 967 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጭ ሲሆን፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ የኃይል ማመንጨት አቅሟን በእጥፍ ያሳድገዋል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img