Friday, November 22, 2024
spot_img

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ጉዳይ ለመምከር በመጪው ሰኞ ወደ ኬንያ ያቀናሉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 3 2014 ― የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶን ብሊንክን በኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ ጉዳይ ለመምከር በመጪው ሰኞ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል፡፡

አንቶንዮ ብሊንክን በኬንያ በሚያደርጉት ቆይታ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባል የሆነችው ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሯት ኬንያ፣ ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው ጄፍሪ ፌልትማንን ማስተናገዷ ይታወቃል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ የተገኙት ፌልትማን፣ ኬንያ የተመለሱት አዲስ አበባ ደርሰው እንደነበር ተነግሯል፡፡

አሁን አንቶንዮ ብሊንክንን የሚቀበሉት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግብዣ ዋይት ሐውስ ተገኝተው ነበር፡፡

ኡሁሩ ከቀናት በፊት በጽሕፈት ቤታቸው በኩል በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት መካከል በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶን ብሊንክን ሰኞ በሚጀምሩት ጉዞ ከኬንያ በተጨማሪ፣ ናይጄሪያ እና ሴኔጋልን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ብሊንክን በአገራቱ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ጉዳይ ከመምከራቸው ሌላ ሽብርተኝነትን ለመመከት የሚደረጉ ትብብሮችን የማደስ አላማ እንዳላቸው አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img