Tuesday, November 26, 2024
spot_img

ሳፋሪኮም በጸጥታ ስጋት ሠራተኞቹን ከአዲስ አበባ እንዳስወጣ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ረቡዕ ኅዳር 1 2014 ― በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ለመግባት እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም፣ በጸጥታ ስጋት ሰበብ ሠራተኞቹን ከአዲስ አበባ እንዳስወጣ ተነግሯል፡፡

የኬንያው ዴይሊ ቢዝነስ እንደዘገበው ከሆነ፣ ኩባንያው ሠራተኞቹን ከአዲስ አበባ ያስወጣው በሁለት ዙር ባለፈው ሳምንት ረቡእ እና ዐርብ ነው፡፡

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሠራተኞቹን ያስወጣው ሳፋሪኮም፣ በኢትዮጵያ አገልግሎት እጀምራለሁ ያለው በመጪው ጥር ወር ነው፡፡

በተጠናቀቀው ጥቅምት ወር ተባብሶ የቀጠለውን የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ከተሞችን አልፈናል ያሉት የሕወሓት ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ እናቀናለን ማለታቸውን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ዜጎቻቸው እንዲወጡ ጥሪ ሲያስተላልፉ ሰንብተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img