Tuesday, November 26, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት ዘጠኝ ያህል ሠራተኞቹ በአዲስ አበባ ታስረውብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 30፣ 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘጠኝ ያህል ሠራተኞቹ በአዲስ አበባ ታስረውብኛል ሲል አስታውቋል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፈርሐን ሐቅን ጠቅሰው የተለያዩ ዓለም ረቀፍ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ የመንግስታቱ ድርጅት ሠራተኞቹ እንዲለቀቁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ሠራተኞቹ በቁጥጥር ስር ለመዋላቸው የተጠቀሰ ምክንያት ባይኖርም የድርጅቱ የፀጥታ ባልደረቦች የታሠሩበት ሄደው እንዳገኟቸው ተገልጿል።

መንግስትም ስለ ሠራተኞቹ እስር ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ሰአት ድረስ ያለው ነገር የለም።

መንግስት ከዚህ ቀደም በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል ያላቸውን ሰባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኞችን ከአገር ማባረሩ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img