Monday, September 23, 2024
spot_img

በፋኖ አደረጃጀት ያለ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል በመንግሥት መዋቅር ስር እንዲገባ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 30 2014 – የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት በፋኖ አደረጃጀት ለሰለጠኑና ወደ ጦር ግንባር የመዝመት ፍላጎት ላላቸው ማንኛውም የታጠቀ ኃይል በመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንዲገቡ ጠይቋል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ባወጣው መግለጫ በአደረጃጀቱ ስር ለሰለጠኑና ለሚዘምቱ አስተዳደሩ ማንኛውም የሎጅስቲክ ድጋፍ አቀርባለሁ ብሏል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በፀጥታ ምክር ቤቱ ወይም በሰላምና ደኅንነት ቢሮ ስምሪት ሳይቀበል መሳሪያ ታጥቆ በከተማዋ በተለያዩ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ይዞ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ተጠያቂ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ ያልተመዘገበ ማንኛውም የግል የጦር መሳሪያ በየአካባቢው በሚገኙ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት እንዲያስመዘግቡ የጠየቀው ኮማንድ ፖስቱ፣ ይኸው የሚመለከታቸው ሰዎች ከትላንት ጥቅምት 29 እስከ ኅዳር 5፣ 2014 ባሉት አምስት ቀናት ተመዝግበው እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ወደ መጠለያ ካምፕ ለማይገቡ ማንኛውም አከራይ የተከራይ ግለሰቦችን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቅ አለባቸው የተባለ ሲሆን፣ ኮማንድ ፖስቱ ለዚህ ምክንያት የጠቀሰው ‹‹በተፈናቃይ ስም ሰርጎ ገቦች›› እንዳሉ ስለተደረሰበት እና ለከተማዋም ደኅንነት የሚል ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img