Monday, September 23, 2024
spot_img

ሕወሓት በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ አዲስ አበባ ላይ ሌላ ጉዳይ የለውም ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 29፣ 2014 ― በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና  የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ  ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም፣ ፒያሳም የተለየ ቀጠሮ የለንም” ሲሉ ተደምጠዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ መቐለ ተገኝተው ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን ያነሱት አቶ ጌታቸው ፤ የንግግሩ ይዘት  በሂደት ያለ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። 

በሌላ በኩል የሕወሃት ቃል አቃባዩ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸው ከአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ታገኛላችሁ ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ትግራይ በከበባ ውስጥ ናት በምን ይደግፉናል ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ኃይላቸው በአማራ ክልል ይፈፅማቸዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም አስተባብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img