Thursday, November 21, 2024
spot_img

ኢሰመኮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ‹‹ማንነትን መሠረት ባደረገ በሚመስል ሁኔታ›› እስር መከናወኑ አሳስቦኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 29 2014 ― የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመላው ኢትዮጵያ ከታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ‹‹ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ›› ሰዎች እያታሰሩ መሆኑን ገልጧል፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀበት ጥቅምት 23፣ 2014 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል።

በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሕግ አስከባሪዎች ‹‹ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራሉ ተብለው ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠሩ ሰዎችን›› መያዝን ቢፈቀድም፤ እስሩ ‹‹ማንነትን/ብሔርን መሰረት ያደረገ በሚመስል መልኩ መከናወኑ፣ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቤተሰብ ጥየቃ፣ ልብስና ስንቅ ማቀበል መከልከሉ እንዲሁም እስሩ ሕጻናት ልጆች ያሏቸው እናቶች አረጋዊያንን ጭምር ያካተተ መሆኑ›› አሳስቦኛል ብሏል።

ኢሰመኮ የህግ አስከባሪ አካላት ‹‹የህጋዊነት፣ የጥብቅ አስፈላጊነትና ተመጣጣኝነት እንዲሁም ከመድልዎ ነጻ መሆን›› የሚሉ መርሆዎችን ሊያከብሩ ይገባል ያለ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የህግ አስከባሪ አካላት ‹‹በማንኛውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ተግባራቶቻቸውንም በከፍተኛ የሙያ ስነምግባር በመመራት የማከናወን ኃላፊነት አለባቸው›› ሲል አሳስቧል።

ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 23፣ 2013 የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት የሚቆይ ስለመሆኑ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img