Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ትዊተር በኢትዮጵያ በዘመቻ መልክ መነጋገሪያ አጀንዳ የሚፈጥርበትን አገልግሎት አቆመ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 27 2014 ― ከዓለማችን ግዙፍ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች አንዱ የሆነው ትዊተር በኢትዮጵያ በዘመቻ መልክ መነጋገሪያ አጀንዳ የሚፈጥርበትን አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ያመለከተው ኩባንያው፣ በማኅበራዊ መድረኩ የሚካሄዱ የመልእክት ልውውጦች ላይ አተኩሮ እየሠራ ስለመሆኑም ነው የገለጸው፡፡

ትዊተር ሁከትን ማበረታታት እና ሰዎችን ማዋረድ ከኩባንያው ህግ ውጪ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በርከት ያሉ ዘመቻዎ የሚስተናገዱበት ትዊተር ኩባንያ፣ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ጋር የተገናኙ አካውንቶችን አግዷል በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከሰሞኑ አቅም ያላቸው ዜጎች ሁሉ ማንኛውንም መሳሪያ ይዘው የሕወሃትን ጥቃት ለመቀልበስ እንዲዘምቱ በግል ትዊተር ገጻቸው ጥሪ ያቀረቡበት መልዕክት የሥነ ምግባር ፖሊሲውን እንደጣሰ አስታውቋል። ኩባንያው የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ከማጥፋት ይልቅ፣ መልዕክቱ የኩባንያውን የስነ ምግባር ፖሊሲ የጣሰ መሆኑን የሚገልጥ መግለጫ ከመልዕክቱ ጋር ማያያዝ እንደመረጠ ገልጧል።

ሌላኛው የማህበራዊ ትስስር መድረክ አቅራቢ ሜታ ኩባንያም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመሳሳይ መልእክት ‹‹ሁከትን ያበረታታል›› በማለት ከፌስቡክ ማኅበራዊ ትስስር ዘዴ ማጥፋቱ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img