Sunday, September 22, 2024
spot_img

ቱርክ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት መካከል አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 27፣ 2014 ― ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን የሚመሯት ቱርክ፣ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቃለች፡፡

አገሪቱ ተባብሶ የቀጠለውን ውጊያ እየተከታተለች መሆኑን ያመለከተው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና ተፋላሚ አካላት ለንግግር እንዲቀመጡ ሁሉንም ድጋፍ ለማድረግ ቱርክ ዝግጁነት እንዳላት አሳውቋል፡፡

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራት ታሪካዊ እና ባሕላዊ ትስስር ተጠብቆ መሄድ የሁልጊዜም የቱርክ መሻት መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ አገሪቱ በኢትዮጵያ ውጊያው ከጀመረ አንስቶ የምታደርገውን ድጋፍ መቀጠሏንም አስታውሷል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ኤርዶጋን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ቱርክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ኢትዮጵያ እያለፈችበት ያለውን ሒደት ‹‹ስሱ›› መሆኑን እንዲሁም ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው፣ ለአገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ አመልክተው ነበር፡፡

በሌላ በኩል ቱርክ በቅርቡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖችን ለኢትዮጵያ ሳትሸጥ እንዳልቀረች ሲነገርባት ነበር፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img