Friday, November 22, 2024
spot_img

ሕወሓት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ጨምሮ 9 ኃይሎች የፖለቲካ ግንባር ሊፈጥሩ መሆኑ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― ሕወሓት እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለውና በመንግስት ሸኔ ተብሎ የሚጠራውን ቡድን ጨምሮ ዘጠኝ ኃይሎች የፖለቲካ ግንባር ሊፈጥሩ መሆኑን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ከሕወሓት እና የኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በአሜሪካ ዋሺንግተን በዛሬው እለት ግንባር ይፈጥራሉ የተባሉት ኃይሎች የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያው አንድነት ግንባር፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ነጻነት ሠራዊት፣ የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር እና የሶማሌ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር መሆናቸው ነው የተገለጸው።

በዛሬው እለት ስምምነት ይፈጥራሉ ከተባሉት ዘጠኝ ኃይሎች መካከል ሁለቱ ማለትም ሕወሓት እና ‘የኦሮሞ ነጻነት ጦር’ በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ናቸው።

ከወራት በፊት ጥምረት መፍጠራቸውን ያሳወቁት ሁለቱ ኃይሎች ከሰሞኑ ሕወሓት ከፌዴራል መንግስት ጋር በሚያደርገው ጦርነት ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሬያለሁ ማለቱን ተከትሎ በጋራ ወደ አዲስ አበባ የማቅናት ፍላጎት እንዳላቸው ሲያሳውቁ ነበር።

ሁለቱ ኃይሎች በዋሺንግተን ከሌሎች አካላት ጋር ሊፈጥሩት አቅደዋል የተባለው ግንባር ግብ የሽግግር መንግስት ለመመስረት መሆኑን ብሉምበርግ የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ነግሮኛል ብሎ ዘግቧል።

በርካታ የታጣቁ ኃይሎችን ስላካተተው ስምምነት በመንግስት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

አንድ ዓመት በደፈነው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ሲወተውቱ ይስተዋላል። አሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛዋ ጄፍሪ ፌልትማንን ወደ አዲስ አበባ መላኳ መነገሩ ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img