አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አስተላልፏል።
ሠራዊቱ ለቀድሞው አባላት ጥሪውን ያደረገው “ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት” መሆኑን ገልጿል።
በዚሁ መሠረት ይህን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ሠራዊቱ ለሚቀላቀሉት የቀድሞ አባላት መስፈርቶችን ያስቀመጠ ሲሆን፣፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ አባላት ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 15፣ 2014 መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።
በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል የሚካሄደውና አንድ ዓመት የደፈነው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ ይታወቃል።