አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ጉዳይ እደሚሰበሰብ ተነግሯል፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚሰበሰበው በተያዘው የፈረንጆች ኅዳር ወር ፕሬዝዳንትንቱን በተቀበለችው ሜክሲኮ ጠያቂነት ነው ተብሏል፡፡
ይኸው የሜክሲኮ ጥያቄ በአየርላንድ፣ ኒጀር፣ ኬንያ እና ሴንት ቪንሴንት እና ግሬናዲንስ ድጋፍ አግኘቷል፡፡ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሚደረግ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት አንድ ዓመት በደፈነው የትግራይ ጦርነት ከዚህ ቀደም ለአስር ጊዜያት ተሰብስቧል፡፡
በምክር ቤቱ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ መቀጠሉን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የጸጥታውን ምክር ቤት ባለፈው ወር በፕሬዝዳንትነት የመራችው የምሥራቅ አፍሪካዋ አገር ኬን እንደነበረች ይታወቃል፡፡