Tuesday, November 26, 2024
spot_img

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ለመምከር ለምሥራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 25፣ 2014 ― የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለምምከር ለምሥራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሙሴቪኒ የአጋቱን መሪዎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንምከር ብለው ቀጠሮ ያስያዙት ለኅዳር 7፣ 2014 መሆኑን ሬውተርስ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር እየተገናኙ ስለመሆናቸው የተነገረላቸው ሙሴቪኒ፣ በተቃራኒው ለተኩስ አቁም እና ድርድር እምቢታውን ገልጧል የተባለው ሕወሓት ጉዳይ አሳስቦኛል ማለታቸውም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማሸማገል ከዚህ ቀደም የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ከሰሞኑ በመፈንቅለ መንግስት የተወገዱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒትር ዐብደላ ሐምዶክ የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻርን ወደ ኢትዮጵያ መላካቸው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተነግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የማቻር ሽምግልና ምን እንደደረሰ የተነገረ ነገር አልነበረም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img