Sunday, September 22, 2024
spot_img

አዲስ ለተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ እየተካሄደ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 24፣ 2014 ― የደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ ለተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ እያካሄደ ይገኛል።

በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው አዲሱን ክልል ያቋቋሙት እና በደቡብ ክልል ስር ያሉት አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አዲሱን ክልል በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተሰበሰበው የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልና ህዝበ ውሳኔ ውጤቱን ማጽደቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ 11ኛ ክልል የሆነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝበ ውሳኔ የተካሄደው ባለፈው መስከረም ወር መገባደጃ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img